የኮለጁ ፕሮግራም ዝርዝር

ለዘላቂ የአገልግሎት ተፅዕኖ ተብሎ የተዘጋጀ ጥልቅ ጥናት።

የሰርተፊኬት ፕሮግራም

ለአንድ ዓመት የሚቆየው የሰርተፊኬት ፕሮግራማችን፣ ለአገልግሎት መሰረት የሚጥልና በጌታ ቃል የታጠቀ ትውልድን ለማፍራት የተዘጋጀ ነው።

የሚወስደ ግዜ - ኣንድ ዓመት
የሚቀጥለው ምዝገባ - July 15, 2026

የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ ኮርስ

ከፍጥረት ጀምሮ እስከ መሲሁ መምጣት ድረስ ያለውን የእግዚአብሔርን የማዳን ታሪክ በጥልቀት የሚመረምር ነው። በዚህ ጥናት ተማሪዎች በ39ኙ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የተገለጡትን ዋና ዋና ጭብጦች፣ ታሪካዊ ዳራዎችና ትንቢታዊ መልእክቶች ይረዳሉ። ኮርሱ የብሉይ ኪዳን እውነቶች ለአዲሱ ኪዳን መረዳት እንዴት መሰረት እንደሚሆኑና ለዛሬው መንፈሳዊ አገልግሎት ያለውን የማይተካ ፋይዳ ያሳያል።

የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ ኮርስ

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት፣ አገልግሎት፣ ሞትና ትንሳኤ እንዲሁም የቤተክርስቲያንን አጀማመር በጥልቀት የሚያጠና ነው። በዚህ ጥናት ተማሪዎች በ27ቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የተገለጡትን ዋና ዋና ወንጌላዊ ጭብጦች፣ የሐዋርያትን መልእክቶችና የክርስቶስን ዳግም ምጽዓት ተስፋ ይረዳሉ። ኮርሱ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች በክርስቶስ እንዴት ፍጻሜ እንዳገኙና የአዲስ ኪዳን እውነቶች ለዛሬው የክርስቲያን ሕይወትና ለአገልግሎት ያላቸውን መሠረታዊ ፋይዳ ያሳያል።

የዲፕሎማ ፕሮግራም

ይህ የሁለት ዓመት የዲፕሎማ ፕሮግራም፣ ተማሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እንዲበስሉና በቤተክርስቲያን ውስጥ ውጤታማ መሪዎች እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ፕሮግራሙ ጥልቅ ቲዎሎጂን ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር በማጣመር ጥራት ያለው ትምህርት ይሰጣል።

የሚወስደው ግዜ: 2 ዓመት  |  የሚቀጥለው ምዝገባ: July 15, 2026

ዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶች (Core Curriculum)

  • የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም (Hermeneutics)
  • የቤተክርስቲያን ታሪክ (Church History)
  • የስብከት ጥበብ (Homiletics) (Preaching)
  • ወንጌል ስርጭት (Evangelism)
  • መንፈሳዊ ስብዕና ግንባታ (Spiritual) Formation
  • ሥርዓተ-መለኮት (Systematic Theology)

የዲግሪ ፕሮግራም

ይህ የ5 ዓመት የዲግሪ ፕሮግራም በተለይ ለወደፊት የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ አስተማሪዎችና ወንጌላውያን የተዘጋጀ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ነው። ፕሮግራሙ ተማሪዎች ጥልቅ የቲዎሎጂ እውቀት እንዲኖራቸው ብቻ ሳይሆን፣ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ በብቃት መምራት የሚችሉበትን ስልታዊ አመራር (Strategic Leadership) እንዲላበሱ ያደርጋል። የአራቱ ዓመታት የጥናት ጉዞ፦ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት (መሠረት እና ጥልቀት)፦በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ መሠረቶች፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ ቋንቋዎች መግቢያ፣ እና ስልታዊ ቲዎሎጂን ትማራለህ። ይህም ለማንኛውም አገልግሎት ጠንካራ መሠረት ይጥልልሃል። 3ኛ እና 4ኛ ዓመት (ልዩ ትኩረት እና አመራር)፦በመጨረሻዎቹ ዓመታት ትኩረቱ ወደ ከፍተኛ አመራር፣ ማህበራዊ ሳይንስ እና የምርምር ሥራዎች (Thesis) ይዞራል። ተማሪዎች በመረጡት ዘርፍ (ለምሳሌ፦ በወጣት አገልግሎት፣ በቤተክርስቲያን አመራር ወይም በተልዕኮ) ላይ ልዩ ትኩረት አድርገው ያጠናሉ። የዲግሪው ፕሮግራም ልዩ ጥቅሞች፦የምርምር ብቃት፦ ሃሳቦችን የመተንተን፣ የመመርመር እና አዳዲስ መፍትሄዎችን የማፍለቅ ችሎታ። ስልታዊ መሪነት፦ ድርጅቶችን ወይም አብያተ ክርስቲያናትን በራዕይ እና በዕቅድ የመምራት ብቃት። ዓለም አቀፍ እይታ፦ ወንጌልን ከተለያዩ ባህሎች እና ማህበረሰቦች አንጻር የመረዳት ስፋት።

የሚወስደው ግዜ: 5 ዓመት)  |  የሚቀጥለው ምዝገባ: July 15, 2026

የፓስተራዊ አገልግሎት


በትምህርተ ስብከት፣ በምክር አገልግሎት እና በቤተክርስቲያን አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ዓለም አቀፍ ተልዕኮ

ባህላዊ ልዩነቶችን ያገናዘበ ተግባቦት እና የወንጌል ስርጭት ስልቶችን ያጠናል።

ክርስቲያናዊ የምክር አገልግሎት

ለአእምሮአዊ እና ለመንፈሳዊ ጤንነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መፍትሄዎችን ይሰጣል።

2026/2027 የትምህርት ዓመት ካሌንደር

የሰርተፊኬት፣ የዲፕሎማ እና የዲግሪ ፕሮግራሞች ።

የሰርተፊኬት ፕሮግራም

የኮርሶች ቅደም ተከተል የኮርስ ስም ሐሙስ
6:00 PM - 9:00 PM
ቅዳሜ
10:00 AM - 1:00 PM
መምህራን
1 የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ September 17, 24
October 1, 8, 15
September 19, 26
October 3, 10, 17
ዶ/ር ጌታቸው
2 መንፈስ ቅዱስና ስጦታዎቹ
Holy Spirit and His Gifts
October 22, 29
November 5, 12, 19
October 24, 31
November 7, 14, 21
ወንድም አበራ
3 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቀኖና
Doctrine
November 26
December 3, 10, 17
November 28
December 5, 12, 19
ፓ/ር ወርቁ
ከ December 21, 2026 እስከ January 13, 2027 — የፈረንጅ አዲስ ዓመትና የኢትዮጵያ የክርስቶስ ልደት ዝግ ጊዜ
4 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኪዳናት
Bible Covenants
January 14, 21, 28
February 4, 11
January 16, 23, 30
February 6, 13
ዶ/ር ሐዋኒ
5 ራስን መስጠት
Submission
February 18, 25
March 4, 11, 18
February 20, 27
March 6, 13, 20
—
6 የሮሜ መልእክት March 25
April 1, 8, 15, 22
March 27
April 3, 10, 17, 24
ዶ/ር ጽዮን
7 በመንፈሳዊነት ማደግ
Spiritual Growth
April 29
May 6, 13, 20, 27
May 1, 8, 15, 22, 29 ወንድም እሸቱ
8 የመጨረሻው ዘመን
The End Time
May 27
June 3, 10, 17, 24
May 29
June 5, 12, 19, 26
ዶ/ር ጌታቸው

የዲፕሎማ ፕሮግራም

የኮርሶች ቅደም ተከተል የኮርስ ስም ሐሙስ
6:00 PM - 9:00 PM
ቅዳሜ
10:00 AM - 1:00 PM
መምህራን
1 አዲስ ጅማሮ
New Beginnings
September 17, 24
October 1, 8, 15
September 19, 26
October 3, 10, 17
ፓ/ር ወርቁ
2 የሐዋሪያት ሥራ
Acts
October 22, 29
November 5, 12, 19
October 24, 31
November 7, 14, 21
ወንድም ምህረተአብ
3 እምነት
Faith
November 26
December 3, 10, 17
November 28
December 5, 12, 19
ፓ/ር አማኑኤል
ከ December 21, 2026 እስከ January 13, 2027 — የፈረንጅ አዲስ ዓመትና የኢትዮጵያ የክርስቶስ ልደት ዝግ ጊዜ
4 መለኮታዊ ፈውስ
Divine Healing
January 14, 21, 28
February 4, 11
January 16, 23, 30
February 6, 13
ፓ/ር አማኑኤል
5 የመሪነት መርሆዎች
Principles of Leadership
February 18, 25
March 4, 11, 18
February 20, 27
March 6, 13, 20
ወንድም አበራ
6 የፀሎት መርሆዎች
Principles of Prayer
March 25
April 1, 8, 15, 22
March 27
April 3, 10, 17, 24
ወንድም ተሾመ
7 ስነ አሰባበክ
Preaching
April 29
May 6, 13, 20, 27
May 1, 8, 15, 22 ዶ/ር ጌታቸው
8 ጽድቅ
Righteousness
May 27
June 3, 10, 17, 24
May 29
June 5, 12, 19, 26
ወንድም ምህረተአብ

የዲግሪ ፕሮግራም

የኮርሶች ቅደም ተከተል የኮርስ ስም ሐሙስ
6:00 PM - 9:00 PM
ቅዳሜ
10:00 AM - 1:00 PM
መምህራን
1 የቆሮንቶስ መጽሐፍ ትምህርት
Corinthians
September 17, 24
October 1, 8, 15
September 19, 26
October 3, 10, 17
ወንድም ምሕረትኣብ
2 ትምህርተ ድኅነት October 22, 29
November 5, 12, 19
October 24, 31
November 7, 14, 21
ዶ/ር ጌታቸው
3 የእግዚአብሔር መንግስት
Kingdom of God
November 26
December 3, 10, 17
November 28
December 5, 12, 19
ዶ/ር ጌታቸው
ከ December 21, 2026 እስከ January 13, 2027 — የፈረንጅ አዲስ ዓመትና የኢትዮጵያ የክርስቶስ ልደት ዝግ ጊዜ
4 መጽሐፈ ዳንኤል January 14, 21, 28
February 4, 11
January 16, 23, 30
February 6, 13
ዶ/ር ጌታቸው
5 የቤተክርስትያን ታሪክ 1
Church History 1
February 18, 25
March 4, 11, 18
February 20, 27
March 6, 13, 20
ዶ/ር ጌታቸው
6 የቤተክርስትያን ታሪክ 2
Church History 2
March 25
April 1, 8, 15, 22
March 27
April 3, 10, 17, 24
ዶ/ር ጌታቸው
7 የምርምር ጽሁፍ አጻጻፍ April 29
May 6, 13, 20, 27
May 1, 8, 15, 22 ፓ/ር ወርቁ
8 የመመረቂያ ጽሑፍ/የወንጌል ተልእኮ May 27
June 3, 10, 17, 24
May 29
June 5, 12, 19, 26
ፓ/ር ወርቁ
የኮሌጁ የ2026/2027 የትምህርት ዓመት የምረቃ ቀን August 29, 2027 ነው። መልካም የትምህርት ዓመት!

የኮሌጁ አመራር

ዶ/ር ጌታቸው

ፓስተር ዶ/ር ሐንፍሬ አሊጋዝ

IEECBC ፕሬዚዳንት

ውድ ተማሪዎች!


በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም እላችኋለሁ፡፡ በቤተክርስትያናችን አመራርና አስተማሪዎች ስም እንኳን ደህና መጣችሁ እላችኋለሁ፡፡ ለመማር መወሰናችሁ ለክርስትና ህይወታችሁ ማደግ ታለቅ ውሳኔ እንደሆነ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ እንኳን ለዚህ ውሳኔ እግዚአብሔር አበቃችሁ፡፡ በትንቢተ ሆሴህ 4፡6 ላይ እንደዚህ የሚል ቃል ተጽፎአል፣ “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።” በእግዚአብሔር ቤት ላሉና ከትምህርት ጋር በተያያዘ ይኸ ቃል ጠንካራና የሚያስፈራ ቃል ነው፡፡ የሚናገረው ስለእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡ የሚለውም የሚከተለውን ነው፡፡ • የእግዚአብሔርን እውቀት ያጣ የጠፋ ነው • የእግዚአብሔርን እውቀት የጠላ የአምላኩን ህግ ይረሳል • የአምላኩን ህግ የረሳ ካህን አይሆንም • ልጆቹም በእግዚአብሔር ይረሳሉ እግዚአብሔር ከዚህ ይጠብቀን፡፡ ከነዚህ ነገሮች ለመዳን መማር ያለብን አሁን ነው። ነገ ይረፍዳል። ይኸን እግዚአብሔር የሰጠንን አሁንን በመጠቀም ትምህርታችሁን በትጋትና ያለማቋረጥ እስከመጨረሻው እንድትማሩ አሳስባችኋለሁ፡፡ የምንማረውን እያሰላሰልንና እየተገነዘብን ካልታዘዝንና በተግባር ካላዋልነው መንፈሳዊ ጠቀሜታ እንደሌለውም ላሳስባችሁም እፈልጋለሁ፡፡ ቃሉን ሰምታችሁ፣ ልክ ቃሉ እንደሚለው እንደዛ ካልታዘዛችሁ የተሰጣችሁን የቤት ስራ ሰርታችሁና ፈተናውን ተፈትናችሁ ስትጨርሱ እንዲሁ በከንቱ ሊረሳ ይችላል፡፡ ይኸን አስመልክቶ የእግዚአብሔር ቃል በያዕቆብ 1፡33-35 እንደዚህ ይላል፣ “ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል። ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።” አሁንም በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ቃሉን ሰምተው የሚታዘዙት በማቲዎስ 7:24-25 ላይ እንደተገለጠው የሚከተለውን ይመስላሉ፡፡ “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።” በዚህ ትምህርት ሂደት ውስጥ ከዲያብሎስ አሰራር፣ ከአለም ማነቆና አቅጫጭነት፣ ከስጋችሁ እስር ያመለጣችሁና የምታስመልጡ፤ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ላይ የተተከላችሁ፣ የጸናችሁና የምታጸኑ፤ በሁለመናችሁ የተባረካችሁና በረከት የምትሆኑ እንድትሆኑ ጸሎቴም ነው ተስፋም የማደርገው ነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!

>ዶ/ር ኣስተማሪ

ዶ/ር ጌታቸው ብሩ

IEECBC ዳይረክተር

ወደዚህ ኮሌጅ ለመማር ሲመጡ እኛ የምናዮት በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ድነው በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እንዳለ ብልትና ካህን ነው። ከዚህም የተነሳ ወደዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ለመማር ሲመጡ ብዙ የሚያውቁት ነገር እንዳለ እናውቃለን፡፡ ብዙ የሌሎች ጸጋ የሚያስፈልጎትም ብልት ኖትና ያለዎትን ሲያካፍሉ የሌሎትን ደግሞ ሲቀበሉ ክርስትያናዊ መንፈሳዊ እድገት እንደሚኖሮት እንገነዘባለን፡፡ በዚህ ቦታ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው የሚገናኙት፣ አስተማሪዎችም ከተማሪዎች ጋር የሚገናኙት በአጋጣሚ እዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሔር ያዘጋጀልን በመገናኘታችን የሚገለጥ መንፈሳዊ እድገትና በረከት አለ፡፡ እርስዎ የዚህ እድገትና በረከት ተካፋይ ስለሆኑ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ እንኳንም ደህና መጡ፡፡ እንድናገለግልዎት ስለፈቀዱም ደስ ብሎናል፡፡


የሚማሩት የመጽፍ ቅዱስ ትምህርት ስለሆነ በዚህ የመማር የማስተማር ሂደት ውስጥ ከዓለምም ሆነ ከዲያብሎስ እንዲሁም ከራስዎ ጋር ያለው ትግል ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ በዓለም በስጋ እስካሉ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል፡፡ እስካሁን ያለውን ትግል አሸንፈው ምዝገባዎን አጠናቀው ለመማር ስለመጡ ደስ ይበሎት፡፡ እሰከመጨረሻው ግን ጸንተው መቆም እንዳለቦት አይርሱ፡፡ እግዚአብሔር ለመማር ከሚያደርጉት ውሳኔዎ ጋር አብሮ ይሆናል፡፡ አብረንዎትም እንጸልያለን፡፡ ማሸነፍን የሚማርና ማሸነፍ አይቀሬ መሆኑን የሚያውቅ ሰው በድል መንገድ ላይ የሚያጋጥሙት መሰናክሎችና ትግሎች ጊዜአዊና የሚሸነፉ እንደሆነ ያውቃል፡፡